የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይን የማፅዳት መርሀ ግብር ተከናወነ - ኢዜአ አማርኛ
የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይን የማፅዳት መርሀ ግብር ተከናወነ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2016 (ኢዜአ)፦ የደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይን የማፅዳት መርሀ ግብር ተከናውኗል።
በፅዳት ዘመቻውም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የተለያየ እምነት ተከታይ የሆኑ ሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በዚሁ ወቅት አቶ ጥራቱ በየነ እንዳሉት፣ የዘመቻው ዋና አላማ ከጽዳት ባሻገር ቦታው ላይ ተገኝተን በዓሉን ለሚያከብሩ ወገኖች ያለንን አብሮነት ለማሳየት ነው።
በዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ አብሮነትን በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር የመዲናዋ ነዋሪዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የመጡ የሃይማኖት አባቶች ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ2016 ዓ.ም የመስቀል በዓል አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።