3ተኛዉ አለም አቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
3ተኛዉ አለም አቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 14/2016 (ኢዜአ)፦ 3ተኛዉ አለም አቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው::
ጉባኤው በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት አዘጋጅነት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አለም አቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል::
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የአንድ ሀገር የብልፅግና ጉዞ እውን ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል የጤና አገልግሎት ስርዓቱን ማዘመን አንዱ መሆኑን ገልጸዋል::
በመሆኑም የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎትም ይህን እውን ለማድረግ የመድሃኒት አቅርቦት ስርዓቱ የተሳለጠ እንዲሆን እየሰራ ነው ብለዋል::
ይህ ጉባኤም አለም አቀፍ የመድሃኒት አቅራቢዎችና አምራቾች በዘርፉ ይበልጥ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል::