ቀጥታ፡

የጉራጌ ባህላዊ እሴቶችን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 14/2016 (ኢዜአ)፦ የጉራጌ ባህላዊ እሴቶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር፥ የጉራጌ ዞን በርካታ ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች መገኛ መሆኑን አውስተዋል።

በዞኑ የጉራጌ ክትፎ አዘገጃጀት፣ ባህላዊ የቤት አሰራር፣ የጉራጌ መንደር (ጀፎረ) አሰራር፣ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት (ቕጫ) እና ሌሎች እሴቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞንም እነዚህ የጉራጌ ባህላዊ እሴቶች በዩኔስኮ እንዲመዘገቡለት ለባለስልጣኑ ጥያቄ ማቅረቡን ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንም ጥያቄውን ተቀብሎ ባህላዊ እሴቶቹ በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም