አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ ፤መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች፡፡
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው 49ኛው የጀርመን በርሊን ማራቶን ዛሬ ሲደረግ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአስደናቂ ብቃት አሸንፋለች።
በበርሊን ማራቶን የዓለም ክብረወሰን በማሻሻል ያሸነፈችው አትሌቷ ባለፈው ዓመትም የበርሊን ማራቶንን ማሸነፏ ይታወሳል ፡፡
በወንዶች ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ ርቀቱን በበላይነት አጠናቋል፡፡