የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) በቦንጌ ሽምበቶ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) በቦንጌ ሽምበቶ እየተከበረ ነው

ቦንጋ ፤ መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ የ2016 የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) ቦንጋ ከተማ በቦንጌ ሽምበቶ እየተከበረ ነው።
የካፈቾ የዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) ቦንጋ ከተማ በበዓሉ መከበሪያ ቦታ በቦንጌ ሽምበቶ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በታላቅ ድምቀት መከበር ጀምሯል።
የካፈቾ ብሔር ባህላዊ ምክር ቤት አባላት በባህላዊ አልባሳት አጊጠውና ባህላዊ ስርዓታቸውን በጠበቀ መልኩ በወጣቶችና አረጋዊያን ታጅበው በዓሉ በሚከበሩበት ቦታ ተገኝተዋል።
በአሉ የይቅርታና የዕርቅ እንዲሁም የአብሮነትና አንድነት ተምሳሌት መሆኑ ተመላክቷል፡፡