የ"ጊፋታ" በዓል እሴቶች እንዲለሙ በትኩረት ይሰራል- አቶ ቀጄላ መርዳሳ

ወላይታ ሶዶ ፤መስከረም 13/2016(ኢዜአ)፡- የጊፋታ ባህላዊ እሴቶችና ሀገር በቀል እውቀቶች እንዲለሙና እንዲጠበቁ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ።

የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የመቻቻል እሴት የሆነውን የ"ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው።


 

በዓሉን ለመታደም ወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም የተገኙት የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ እንዳሉት የወላይታ ብሔር የበርካታ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት መሆኑን ተናግረዋል።

ወላይታ ቀደምትና አኩሪ ከሆኑ ትውፊቶች የሚጠቀሱ ባህሎች ባለቤት መሆኑን አንስተው፤ የበዓሉ ባህላዊ እሴቶቹ ለምተውና ጎልብተው መውጣት ይገባቸዋል ብለዋል።

የ"ጊፋታ" በዓል ባህላዊ ቅርሶችና ሀገር በቀል እውቀቶች እንዲለሙና እንዲጠበቁ በሚሰራው ስራ የሚኒስቴሩ  ድጋፍ እንደማይለየው አንስተዋል።

የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ የ"ጊፋታ" በዓል በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በታላቅ ድምቀት በመከበር ላይ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም