ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ከግብጹ አል አህሊ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2016 (ኢዜአ)፦ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2023/24 የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ11 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ የግብጹ አል አህሊ ጋር ዛሬ ያከናውናል።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ 75 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይከናወናል።

አል አህሊ የወቅቱ የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ነው።


 

ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የዛንዚባሩን ኬኤምኬኤም ክለብን በደርሶ መልስ 5 ለ 2 ውጤት ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ፈረሰኞቹ አል አህሊን በደርሶ መልስ ካሸነፉ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባታቸውን ያረጋግጣሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም