ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔድ የተናጥል ማዕቀብን አትደግፍም-አቶ ደመቀ መኮንን - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔድ የተናጥል ማዕቀብን አትደግፍም-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2016 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔዱ የተናጥል ማዕቀቦችን እንደማትደግፍ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።
አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የመንግስታቱ ድርጅት አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሃገራት ላይ የሚካሔዱ የተናጥል ማዕቀቦችንና የኢኮኖሚ ተጽእኖዎችን ትቃወማለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርሆዎችንና ዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጻጸር በመሆኑም ድርጊቶ ሊቆም እንደሚገባ ገልጸዋል።