ቀጥታ፡

የሀድያ ብሄር የዘመን መለወጫ ያሆዴ  በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከበረ ነው

ሆሳዕና፤መስከረም 12/2016 (ኢዜአ)፦ የሀድያ ብሄር የዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ስነ -ሥርዓት ላይ ለመሳተፍ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከተማ መዋቅሮች የተውጣጡ የህበረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችም ታድመዋል።

የያሆዴ በአል በአብሮነትና በመተጋገዝ እንዲሁም በተለያዩ ክንውኖች ደምቆ እየተከበረ ነው።

በዓሉ ለሰላም፣ለሀገር ፍቅር፣ ለአንድነትና አብሮነት መጠናከር በሚኖረው በጎ ገጽታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይትም ተደርጓል።

በዋዜማው የ"አተካን ሂሞ" መርሃ ግብር የተከበረ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የሃድያ ብሔር አለባበስ ደምቀው በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም