በባህርዳር ከተማ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው 

ባህር ዳር ፤ መስከረም 11/2016(ኢዜአ)፡-  በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር  ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላምና የልማት  ውይይት  እየተካሄደ ነው።

 ውይይቱ እየተካሄደ ያለው "ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የሁሉንም አካል ርብርብ ይጠይቃል"  በሚል መሪ ሃሳብ ነው።

በውይይት መድረኩ  የባህር ዳርና አካባቢው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሜጀር ጄኔራል ሙሉአለም አድማሱ፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ጊዜው ታከለ ባቀረቡት ጽሑፍ፤  በነበረው የጸጥታ ችግር ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን  ገልጸዋል።

 ችግሮቹ በሰላማዊ መንገድ በዘላቂነት  የሚፈቱ ናቸው ያሉት ጽሑፍ አቅራቢው፤ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ችግሮች እንዲፈቱ ከህዝቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን  አስረድተዋል።

የውይይቱ ዓላማ  ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ  የህዝቡን ተሳትፎ ለማጠናከር  መሆኑን አስታውቀዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም