የአማርኛ ቋንቋ በሞስኮ ከተማ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀመረ 

565

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 09/2016 (ኢዜአ)፦ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሩሲያ ሞስኮ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል።

የሩሲያው ዜና አግልግሎት ስፑቲኒክ እንደዘገበው አማርኛን ጨምሮ የአፍሪካ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል።

የቋንቋዎቹ  ትምህርት መጀመር  በሩሲያ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ባሕላዊ መስኮች የነበሩ ትስስሮችን ይበለጥ ለማሳድግ ሚናው የጎላ መሆኑን የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተናግረዋል። 

አማርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ቋንቋነት መማር የጀመሩ ተማሪዎች ለስፑቲኒክ እንደተናገሩት፣ የአማርኛ ቋንቋ ከማወቅ ባሻገር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የህዝቡን ባህልና አኗኗር የማወቅ ጉጉት አሳድሮባቸዋል።

ሩሲያ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር እንደምትጀምር ባለፈው ዓመት ማስታወቋ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም