ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊነት የተሞላበት የስደተኞች አያያዝ የሚደነቅ ነው - ፍሊፖ ግራንዲ 

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 8/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊነት የተሞላበት የስደተኞች አያያዝ የሚደነቅ ነው ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲ ገለጹ።

78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ ነው።

አቶ ደመቀ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ግራንዲ ጋር ተወያይተዋል።
 

ፍሊፖ ግራንዲ ኢትዮጵያ በስደተኞች ላይ ያላትን ፖሊሲና የሱዳን ስደተኞችን ከፍተኛ  ሰብዓዊነት በተሞላበት መልኩ ተቀብላ እያስተናገደች ያለችበትን መንገድ አድንቀዋል።

ለጋሽ አካላት በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩም  ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት ልዑካን ጋር የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ስኬታማ ውይይቶችን ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም