በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ አሸነፈ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 6 /2016 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 0 አሸንፏል።

ጎሎቹን ሀብታሙ ታደሰ ከእረፍት በፊት እና በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ አስቆጥሯል።

የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን፤ በደርሶ መልሱ ጨዋታ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናል።

ባህር ዳር ከተማ በመጀመሪያው ዙር ቅድመ ማጣሪያ የታንዛኒያውን አዛም በደርሶ መልስ ጨዋታ ማሸነፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም