ኢትዮጵያ አህጉራዊና አካባቢያዊ የመሠረተ ልማት ትስስሮች ልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ ተመረጠች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ አህጉራዊና አካባቢያዊ የመሠረተ ልማት ትስስሮች ልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ ተመረጠች
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 5/2016 (ኢዜአ) ፡- ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አህጉራዊና አካባቢያዊ የመሠረተ ልማት ትስስሮች ልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ ተመረጠች
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እ.ኤ.አ ከሴፕቴምበር 12-15/2023 በዛንዚባር ታንዛኒያ ሲካሄድ በቆየው 4ኛው የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ 4ኛውን የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴን በሊቀ-መንበርነት እንድትመራ በሙሉ ድምጽ ተመርጣለች፡፡
በ4ኛው የልዩ ቴክኒካል ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት በህብረቱ ኮሚሽን አማካኝነት የሚከናወነው የአፍሪካ የመሠረተ ልማት ፕሮግራም /Program for infrastructure Development/ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት እንዲራዘምም ተደርጓል።
በተጨማሪም ሁሉንም ዓይነት የትራንስፖርት ዘዴ/መንገድ፣ አየር፣ ባቡርና ማሪታይም /የሚመለከቱ ሌሎች መርሀ-ግብሮች መጽደቃቸውን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡