ቀጥታ፡

ከሶስት ዓመታት በፊት የተተከሉት የቡና ዛፎች የአረንጓዴ ዐሻራን ፍሬ እያፈሩ ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶክተር)

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 5/2016 (ኢዜአ) ፡- ከሶስት ዓመታት በፊት የተተከሉት የቡና ዛፎች የአረንጓዴ ዐሻራን ፍሬ እያፈሩ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶክተር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከሶስት ዓመታት በፊት የተተከሉት የቡና ዛፎች የአረንጓዴ ዐሻራን ፍሬ እያፈሩ ነው ብለዋል።


 

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስነ-ምህዳሩን ከማረጋጋት ባለፈ የግብርና ደን ልማትን በማጎልበት ላይ ይገኛል ሲሉም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም