ሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቡሩንዲ ጋር የሚያደረጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 4/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከቡሩንዲ ጋር የሚያደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ በሜዳዋ የምታደርገውን ጨዋታ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደምታከናውን ለካፍ ማሳወቋን ፌዴሬሽኑ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ቡሩንዲ በሜዳዋ ልታደርግ የነበረውን ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው።

የመጀመርያው ጨዋታ መስከረም 9/2016 ሲከናወን፤ ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ መስከረም 15/2016 እንደሚከናወን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም