ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኩባ ሀቫና ገቡ 

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 4/2016 (ኢዜአ) ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን  ከልዑካቸው ጋር በቡድን 77 እና ቻይና የአገራት መሪዎችና መንግስታት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ ኩባ ሀቫና ገብተዋል።

ልዑኩ ሆዜ ማርቲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኩባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎችና በኩባ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ አቀባበል አድርገውለታል።

ጉባኤው ነገ እና ከነገ በስቲያ የሚካሄድ ሲሆን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ወቅታዊ የልማት ፈተናዎችን ለመፍታት ያላቸውን ሚና በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም