የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለፖሊስ አመራርና አባላት የበዓል ስጦታ አበረከተ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለፖሊስ አመራርና አባላት የበዓል ስጦታ አበረከተ
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 1/2016 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሰላምና ደህንነት ለማስፈን በጀግንነት ሲፋለሙ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ ለሚገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት የበዓል ስጦታ አበርክቷል።
ስጦታው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የክልል ፖሊስ አባላት ለሰንደቅ ዓላማና ለአገር ሉዓላዊነት ክብር ሲሉ ለከፈሉት መስዋዕትነት የተበረከተ መሆኑም ተገልጿል።
የአዲስ አመት የበዓል ስጦታውን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ማበርከታቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።