አብሮነት የድሬዳዋ ልዩ መገለጫና ሃብት ነው- ከንቲባ ከድር ጁሃር - ኢዜአ አማርኛ
አብሮነት የድሬዳዋ ልዩ መገለጫና ሃብት ነው- ከንቲባ ከድር ጁሃር
ድሬዳዋ፤ ጳጉሜን 6/2015 (ኢዜአ)፡- አብሮነት የድሬዳዋ ልዩ መገለጫና ሃብት መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ገለጹ።
በ1895 ዓ.ም በታህሳስ ወር ወደ እምብርቷ የዘለቀውና ከጅቡቲ ተነስቶ ድሬዳዋ የገባው የመጀመሪያው ባቡር እንደ ከተማ ለመመስረቷ ዋቢ እንደሆናት ይጠቀሳል።
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እንዲሁም ከባቡር ጋር የመጡ የውጭ አገራት ዜጎች መኖሪያ ሆና አሁን ድረስ ዘልቃለች-ድሬዳዋ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ዛሬ "በህብር የተሰራች ሀገር" በሚል መርህ የተከበረው የአብሮነት ቀን የድሬዳዋ ቀን ነው ብለዋ።
ይህን ልዩ ሃብት እስከ መጨረሻው በመጠበቅና በመንከባከብ ለአገር ህብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከር ማዋል ይገባል ብለዋል።
የድሬደዋ ነዋሪ የሆነው ወጣት ኤሊያስ መሐመድ የድሬዳዋ መገለጫ አብሮነት በሐዘን እና በደስታ፤ በክፉና በደግ ጊዚያት ጭምር ፀንቶ በተግባር የሚገለጽ መሆኑን ገልጿል።
"እኔና ጓደኛዬ ታገል የሁለታችንንም እናቶች ጡቶች ጠብተን ያደግን፤ የትኛውም ክስተት ቢፈጠር አብሮነታችንን የሚሸረሽር አንዳች ነገር እንዳይኖር ተጋምደን የተሰራን ወንድማማቾች ነን" ብሏል።
ይህ የታገመደ አብሮነት ከአያቶቻቸው፤ ከወላጆቻቸው የወረሱት ቅርስና ሃብት መሆኑንም ነው ወጣቱ አስታውቀል።
በድሬዳዋ በግጥም ሥራው የሚታወቀው ሲሳይ ታደሰ በበኩሉ የድሬዳዋ የአብሮነትና የአንድነት መገለጫን "ፈጣሪ ባርኮ ለድሬዳዋ የሰጣት ሃብት ነው" ብሏል።
የድሬን አብሮነት ከገለፀበት ግጥም መካከል ጥቂት ስንኞችን በመምዘዝ "አብሮነት በዕለታዊ ክስተት ጭምር የሚታይና የሚናኝ ውብ እሴት መሆኑን በአፅንቶ አንፀባርቋል።
የ በድሬዳዋ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅንነታቸው፣ የዋህነታቸው፣ ታታሪነታቸው እንዲሁም በአብሮነት መንፈስ ሁሉንም ተግባራት በጋራ ተባብረው መከወናቸው የሚያስደስትና ለሌሎችም አካባቢዎች በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የድሬዳዋ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፀሐፊ ወንድም ሚልኪያስ ታዬተናግረዋል።
ይህን የአብሮነት እሴትን አጠናክሮ ማስቀጠል የሁላችንም ኃላፊነት እና ተግባር ሊሆን ይገባልም ብለዋል።
በድሬዳዋ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ ደምቀው ባከበሩት የአንድነት ቀን ላይ ይህን ልዩ የአብሮነት እሴት ለማጠናከር ተግተው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።