ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለአዲስ አመት  የእንኳን አደረሳችሁ  መልእክት አስተላለፈ

 

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 6/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  አዲሱ አመት የሠላምና የደስታ እንዲሆን በመመኘት ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለመላው የሀገቱ ህዝቦች፣ የኢትዮጵያ  የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ አባላትና ደጋፍዎች እንኳን ከ2015 ዓ.ም ወደ 2016 ዓ.ም አሸጋገራችሁ ብሏል::

በአዲሱ ዓመት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል፣ በመንግስትና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አብሮ የመስራት የፖለቲካ ባህል የሚዳብርበት እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር የጋራ ምክር ቤቱ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግም ጠቅሷል።

“2016 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ሠላምና መረጋጋት የሚፈጠርበት የሠላም፣ የደስታና ተድላ ዓመት እንዲሆን የጋራ ምክር ቤቱ ይመኛል” ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም