ቀጥታ፡

ዕውቁ ዲፕሎማት አቶ ከተማ ይፍሩ የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2015(ኢዜአ)፦ዕውቁ ዲፕሎማት አቶ ከተማ ይፍሩ የዓመቱ የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ ሆኑ።

በ11ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች የተለዩ ኢትዮጵያውያን ተሸልመዋል። በዚህም መሰረት፦ 

በመምህርነት ዘርፍ- አዝማች ይርጋ ገብሬ፣ 

በባህል፣ ቅርስ እና ቱሪዝም ዘርፍ-  የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ 

በንግድ ኢንዱስትሪ እና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ- ኩሪፍቱ ሪዞርትና ስፓ፣

በበጎ አድራጎት- ወይዘሮ እቴነሽ ወንድምአገኘሁ፣

በኪነ ጥበብ (በስዕል ዘርፍ)-ሰዓሊ ወርቁ ጎሹ፣  

መንግስታዊ ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ዘርፍ-ዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው፣ 

በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ-ኤፍሬም እንዳለ፣  

በሳይንስና ቴክኖሎጂ-ዶክተር ሙሉዓለም ገሰሰ፣ 

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዘርፍ-ዶ/ር አሰፋ ጃጃው የዓመቱ በጎ ሰው ተብለው ተሸልመዋል።


 

በዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት ዕውቁ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት አቶ ከተማ ይፍሩ የዓመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።  

አቶ ከተማ ይፍሩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ  ዘመን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን በተለያዩ ኃላፊነት ያገለገሉና ለሀገርና ለህዝብ ትልቅ ሚና የተወጡ ሰው መሆናቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ለአብነትም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲቋቋም፣ በፓን አፍሪካዊነት ማበብ ትልቅ ሚና የተወጡ፣ የአፍሪካ ነፃነት ታጋዮች በኢትዮጵያ እንዲሰለጥኑ  ያደረጉ፣ ሀገራቸውን በፅናት ያገለገሉ ዕውቅ ዲፕሎማት ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም