የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5/2015(ኢዜአ)፦የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የህዳሴውን ግድብ አራተኛ እና የመጨራሻ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቅን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል።
“የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራተኛና የመጨረሻው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት በመከናወኑ የተሰማኝን ከልብ የመነጨ ደስታ እየገለፅኩ ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል።
የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሻራ ያረፈበት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በስኬት የመጠናቀቅ ብስራት በአዲስ አመት ዋዜማ መሰማቱ አዲሱን አመት በብሩህ መንፈስ እንድንቀበለው የሚያደርግ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በአዲሱ አመት ልናከውናቸው ያቀድናቸውን ዘርፈብዙ ስራዎች በመፈፀም ወደ ብልፅግና የምናደርገውን ጉዞ ለማቀላጠፍም ከፍተኛ የሞራል ስንቅ በመሆን ብርታት የሚጨምር መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።