ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ4ኛ ዙር ህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ የደስታ መልእክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ4ኛ ዙር ህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ የደስታ መልእክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 5/2015(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ማለዳ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማብሰራቸውን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች ፤ትቀጥላለች ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ መጪው ጊዜ ብርሃናማ ነው ሲሉ ገልጸዋል።