የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪን በውጤታማነት ለመምራት የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ኃይል በስፋትና በጥራት ማፍራት ይገባል - ሙፈሪያት ካሚል - ኢዜአ አማርኛ
የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪን በውጤታማነት ለመምራት የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ኃይል በስፋትና በጥራት ማፍራት ይገባል - ሙፈሪያት ካሚል
የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪን በውጤታማነት ለመምራት የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ኃይል በስፋትና በጥራት ማፍራት እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ።
ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትምህርት መርኃ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 321 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ በቁጥርም በጥራትም በርካታ የሰው ኃይል የሚጠይቅ ነው።
የሆቴልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዘርፉን በሠለጠነ የሰው ኃይል ለማደራጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
እንዲያም ሆኖ የዘርፉን የአገልግሎት ጥራት ለማረጋገጥ ብዙ መሥራት እንዳለበት ጠቁመው የዛሬ ተመራቂዎች ለዚሁ ሊተጉ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ የቱሪዝም ዘርፍ አጠቃላይ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
ተመራቂዎችም ለዘርፉ አድገት የበኩላቸውን በመወጣት ኢትዮጵያ በዘርፉ ያቀደችውን እቅድ ለማሳካት ትልቅ ግብዓት እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ተመራቂዎች በትምህርት ወቅት የቀሰሙትን እውቀት ለዘርፉ እድገት ሊያውሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ተመራቂዎችም በቀሰሙት እውቀት ለዘርፉ እድገት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ላለፉት 55 ዓመታት በቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ዘርፉን እየደገፈ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም ነው።