ቀጥታ፡

እውነተኛ ነፃነትን ለመጎናፀፍ እናምርት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፤ ጰጉሜን 4/2015(ኢዜአ)፦እውነተኛ ነፃነትን ለመጎናፀፍ እናምርት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በቂ ውሃ፣ በቂ መሬት፣ ከበቂ በላይ ወጣት ኃይል ያላትን ድንቅ ሀገር ከልመና ካላላቀቅናት ነፃነት ዘበት ነው ብለዋል።

እውነተኛ ነፃነት ለመጎናፀፍ እናምርት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንቅ ስራ ጀምረናል፤ ልመናን ታሪክ የሚያደርግ አርበኝነት በግብርና ምርት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም