የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ መልኩ የሚያስከብር የመከላከያ ሃይል ገንብተናል- ሌተናል ጀራል ይመር መኮንን - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ መልኩ የሚያስከብር የመከላከያ ሃይል ገንብተናል- ሌተናል ጀራል ይመር መኮንን
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ መልኩ የሚያስከብር የመከላከያ ሃይል ገንብተናል ሲሉ የመከላከያ የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን ገለጹ።
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በወታደራዊ ጥበብ ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች አስመርቋል።
በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የመከላከያ የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንን፤ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከጥንት እስከ ዛሬ ክብሯንና ሉዓላዊነቷን አስጠብቀው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።
አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ መልኩ የሚያስከብር የመከላከያ ሃይል ገንብተናል ብለዋል።
በዛሬው እለት የተመረቁት ምልምል ወታደሮችም ዘመናዊ ወታደራዊ ትምህርት ወስደው ያጠናቀቁና የሀገራቸውን ክብር ለማስጠበቅ የላቀ ቁርጠኝነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይነትም ጠንካራ የመከላከያ ሃይል የመገንባት ስራ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት ለማወክ የሚጥሩ ሃይሎችን በማስታገስ በየትኛውም ሀገራዊ ተልእኮ በላቀ መልኩ ግዳጅ መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሰራዊት ገንብተናል ብለዋል።
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ጡምሲዶ ፊታሞን፤ ወታደራዊ ጥበብና ስነምግባር የተላበሰ ሰራዊት ማፍራት ላይ ትምህርት ቤቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በምርቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የተመራቂ ቤሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።