ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለተማሪዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የበጎነት ቀንና አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ወላጆቻቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ኢዜአ በመረጃ ተደራሽነት አስተማማኝ የዜና ምንጭ ከመሆን ባለፈ በማህበራዊ ሃላፊነትም የተለያዩ ተሳትፎዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ይሄንንም ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ተማሪዎችና የተማሪዎች ወላጆችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወላጆቻቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ከ2009 ዓ.ም አንስቶ በቋሚነት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ለተማሪዎቹ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣ የምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያና ሌሎች ድጋፎችን አድርጓል።

የበጎነት ቀን "በጎነት ለአገር" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሐ-ግብሮች በመከበር ላይ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም