ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለረጅም ዓመታት በተቋሙ ላገለገሉ ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት የመስጠት መርሃግብር እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2015(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለረጅም ዓመታት በተቋሙ ላገለገሉ ከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት የመስጠት መርሃግብር እያካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ በተቋሙ ለረጅም ዓመታት ላገለገሉ ከፍተኛ መኮንኖችና አመራሮች የሜዳሊያ፣ ሪቫን እና የምስክር ወረቀት እየተሰጠ ይገኛል።


 

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፣ ሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

አየር ሃይል በቢሾፍቱና አካባቢው በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች የበዓል ስጦታ ማዘጋጀቱ ታውቋል።

ጳጉሜን 3 የበጎነት ቀን "በጎነት ለሀገር" በሚል መሪሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ መልካም ተግባራትን በማድረግ በመከበር ላይ ይገኛል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም