ቀጥታ፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሞቃዲሾ ገባ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2/2015 (ኢዜአ)፦ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሞቃዲሾ ገብቷል።

የልዑካን ቡድኑ ኤደን አዴ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሳላህ አህመድ ጃማ እና በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ አቀባበል እንደተደረገላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም