ቀጥታ፡

የመስዋዕትነት ቀን በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2015 (ኢዜአ)፦ የመስዋዕትነት ቀን "በመስዋዕትነት የምትፀና ሀገር " በሚል መሪ ቃል በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ቅጥር ግቢ እየተከበረ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሠ፣ ጄነራል መኮንኖች፣ የፌዴራል የፀጥታ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በበዓል አከባበሩም እስከአሁን ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ክብር ውድ ህይወታቸውን የሠው የሠራዊቱ አባላትና ሌሎች የፀጥታ አካላት የሚዘከሩበት እንዲሁም የሚታወሱበት ዕለት መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም