የመሥዋዕትነት ቀንን ስናከብር የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መሥዋዕትነት ክብር በመስጠት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የመሥዋዕትነት ቀንን ስናከብር የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መሥዋዕትነት ክብር በመስጠት ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2015(ኢዜአ)፦ የመሥዋዕትነት ቀንን “በመሥዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ስናከብር የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መሥዋዕትነት ክብር በመስጠት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ዕለቱን የምናከብረው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገን በመስቀል እና ደም በመለገስ፣ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነታቸው ያጸኑ ጀግኖቻችንን በመዘከር እንዲሁም ሀገር እና ሕዝብን ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ከቆሙ የፀጥታ ኃይሎች አባላት ጎን መቆማችንን በማሳየት ነው” ብለዋል።