ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች ዛሬ ይከበራል - ኢዜአ አማርኛ
ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች ዛሬ ይከበራል
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2015 (ኢዜአ)፦ ጳጉሜን 2 የመስዋዕትነት ቀን በመላው ኢትዮጵያ “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ዛሬ ይከበራል፡፡
ጠዋት 5 ሰዓት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባለበት ቆሞ ቀኝ እጅን ወደ ላይ በማንሳት”እኔ የኢትዮጵያ የፀጥታ፣ የመረጃ እና የደኅንነት ተቋማት ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት ክብር እሰጣለሁ!” የሚል መልዕክት እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት ዘርፍ ለሀገሩ የሚጠበቅበትን መስዋዕትነት ለመክፈል በብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡