ቀጥታ፡

የአገልጋይነት ቀንን አስመልክቶ "ኢትዮጵያን እናገልግል" በሚል መሪ ሃሳብ የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተገኝተው አገልግሎት ሰጡ

አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 1/2015 (ኢዜአ) ፦ የአገልጋይነት ቀንን አስመልክቶ "ኢትዮጵያን እናገልግል" በሚል መሪ ሀሳብ የተለያዩ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተገኝተው  አገልግሎት ሰጡ።

በመርሃ ግብሩም የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሌ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሃይ ጳውሎስ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ዘሀራ ሑመድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

የጳጉሜን ቀናት ስያሜዎችና መሪ ሃሳባቸው ጳጉሜን 1 የአገልጋይነት ቀን ሆኖ "ኢትዮጵያን እናገልግል" በሚል መሪ ሃሳብ ተስይሞ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

ጳጉሜን-2 የመስዋእትነት ቀን በሚል "በመስዋእትነት የምትጸና ሀገር"፣ ጳጉሜን -3 የበጎነት ቀን "በጎነት ለሀገር"፣ ጳጉሜን -4 የአምራችነት ቀን በሚል "ከሸማችነት ወደ አምራችነት"፣ ጳጉሜ-5 የትውልድ ቀን "ኢትዮጵያ የትውልዶች ድምር" በሚል እንዲሁም ጳጉሜን-6 ደግሞ የአብሮነት ቀን "በህብር የተሰራች ሀገር" በሚል መሪ ሀሳቦች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብረው እንደሚውሉ የወጣወው መርሃ-ግብር ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም