በመፍጠርና በመፍጠን ሀብት፣ ዕውቀትና ግብዓት አስተባብረን በትጋት እየሰራን በርካታ ድሎችን ተጎናጽፈናል--ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በመፍጠርና በመፍጠን ሀብት፣ ዕውቀትና ግብዓት አስተባብረን በትጋት እየሰራን በርካታ ድሎችን ተጎናጽፈናል--ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 29/2015 (ኢዜአ) ፡- በመፍጠርና በመፍጠን ሀብት፣ ዕውቀትና ግብዓት አስተባብረን በትጋት እየሰራን የሰው ልጆችን ህይወት የቀየሩ በርካታ ድሎችን ተጎናጽፈናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ "አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የውይይት መርሃ ግብር ከፍተዋል።
ኢትዮጵያ መልከ ብዙ ናት፤ ይህን መልከ ብዙነት በፍቅርና በመከባበር ጌጧ ያደረገችው አዲስ አበባ ከዋና ከተማነት ልቃ የኢትዮጵያ ተምሳሌት ሆናለች ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች በመልዕክታቸውም 14ኛው የኢትዮጵያ የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተን "አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የውይይት መርሃ ግብር ከፍተን ውይይቱን በመምራት ተሳትፈናል ብለዋል።
ጠንካራ የአካታችነት ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እንዲኖር እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መሰል መድረኮች አስተዋጿቸው የላቀ መሆኑንና ለዚህም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።
በመፍጠርና በመፍጠን ሀብት፣ ዕውቀትና ግብዓት አስተባብረን በትጋት እየሰራን የሰው ልጆችን ህይወት የቀየሩ በርካታ ድሎችን ተጎናጽፈናል ሲሉም አክለዋል።
ውጤቶቹ መጪው ትውልድ ጭምር የሚጠቀምባቸው ናቸውና ስለኢትዮዽያ በመስራታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል ከንቲባዋ።
የጎደለውን ለመሙላትና ስኬቶቻችንን ለማላቅ እንዲህ እይነት መድረኮችን በእጅጉ ስለምንፈልጋቸው ተሳታፊዎች ለሚሰጧቸው ሀሳቦችና አስተያየቶች ጆሮአችንም፣ ልባችንም ክፍት ነው ብለዋል።