"አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" የተሰኘው የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ-ርዕይ ዛሬ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
"አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" የተሰኘው የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ-ርዕይ ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 29/2015 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" የተሰኘው የፓናል ውይይት እና የፎቶ ግራፍ አውደ-ርዕይ ዛሬ ይካሄዳል::
መድረኩ "አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት" በሚል ርዕስ የሚካሄድ ሲሆን፤ የፓናል ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ይመሩታል።
የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፣ አቶ አሽኔ አስቲን፣ አቶ ልዑልሰገድ አበበ እና ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የመወያያ ጽሁፎችን በተለያዩ ርዕሶች ላይ እንደሚያቀርቡ ኢፕድ ዘግቧል።