የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት የሚሰጥበት ዓቢይ ቅርንጫፍ ሥራ አስጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት የሚሰጥበት ዓቢይ ቅርንጫፍ ሥራ አስጀመረ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2015 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት የሚሰጥበትና ደንበኞች እራሳቸው የሚስተናገዱበት ዓቢይ ቅርንጫፍ ሥራ አስጀመረ።
በአዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኘውን ዓቢይ ቅርንጫፍ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዛሬ መርቀው ከፍተውታል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በዚህ ዓቢይ ቅርንጫፍ ሁሉም አገልግሎቶች በዲጂታል የሚሰጥበት ነው።
ደንበኞች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው የሚስተናገዱበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
የባንኩ ዓቢይ ቅርንጫፍ መከፈት ለታላላቅና ኮርፖሬት ደንበኞች የሚሰጠውን የአገልግሎት ጥራት ከፍ ማድረግ የሚያስችል መሆኑንም እንዲሁ።
በቅርንጫፉ አዲስ ሒሳብ ለሚከፍቱ ደንበኞች በዲጂታል ሥርዓት ፎቶና ፊርማ የሚቀበል መሆኑንም ተናግረዋል።
ባንኩ በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፉን በማዘመን የዲጂታል ኢኮኖሚን ዕውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።