''መደመር የዘመኑ አርበኝነት'' በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያዘጋጃው ፓናል በጅግጅጋ ከተማ እያተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
''መደመር የዘመኑ አርበኝነት'' በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያዘጋጃው ፓናል በጅግጅጋ ከተማ እያተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2015 (ኢዜአ) ፡- ''መደመር የዘመኑ አርበኝነት'' በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሱማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ፓናል በጅግጅጋ ከተማ እያተካሄደ ነው።
በመድረኩ የፌዴራልና የሱማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በፓናሉ በመደመር እሳቤ ላይ ያተኮሩ አራት የውይይት መነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
የዛሬው መድረክ ሶስተኛው ሲሆን ከዚህ ቀደም ኢዜአ በመደመር ላይ ያተኮሩ ሁለት የፓናል ውይይቶች ማካሄዱ ይታወሳል።