ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ-ቼንግዱ የካርጎ በረራ ጀመረ

 አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 26/2015(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ቻይናዋ ቼንግዱ ከተማ የካርጎ በረራ ትናንት ጀምሯል።

አየር መንገዱ በረራውን መጀመር እንዲሁም በካርጎ ልማት በትብብር መስራት የሚያስችለው ስምምነት ከቻይና መንግስት የዘርፉ ተወካዮች ጋር በቼንግዱ ከተማ ተፈራርሟል።
 

በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲና የቻይና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ቤጂንግ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ60 በላይ ዓለም አቀፍ የካርጎ መዳረሻዎች አሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም