የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ የአመራር ሹመቶችን ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ የአመራር ሹመቶችን ሰጠ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2015(ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በ13/12/2015 ዓ.ም በተካሄደው የክልሉ ምስረታ ጉባኤ ከክልሉ ሕዝብ ምክር ቤት በተሰጠው ውክልና መሰረት የካቢኔ አባላትን ሹመት ሰጥቷል።
በዚህም መሰረት:-
1 አቶ አክሊሉ ለማ - የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2 አቶ ቢረጋ ብርሃኑ - የኢንተርፕራይዝ ልማትና ሥራ ፅ/ፈ/ ቢሮ ኃላፊ
3 ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ - የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
4 ዶ/ር እንዳልካቸው ጌታቸው - ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
5 ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ - የፕላን ቢሮ ኃላፊ
6 አቶ ብርሃኑ ዘውዴ - የከተማና እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7 ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
8 አቶ ግዛቴ ጊጄ - የደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ
9 ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ - የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
10 አቶ ሀ/ማሪያም ተስፋዬ - የግብርና ቢሮ ኃላፊ
11 አቶ አብዩት ደምሴ - የቴክኒካና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ
12 አቶ ተፈሪ አባተ - የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
13 አቶ ታረቀኝ ሀብቴ - የመስኖና ቆላማ አከባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ
14 አቶ ንጋቱ ዳንሳ - የፐቢሊክ ሠርቪስ እና ሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
15 አቶ ተካልኝ ጋሎ - ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
16 አቶ አቤነዘር ተረፈ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
17 አቶ ገለቦ ጎልቶሞ - የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
18 ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ - የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
19 ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን - የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
20 አቶ አርሻሎ አርካል - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
21 ወ/ሪት ፍሬህይወት ዱባለ - የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
22 አቶ እንዳሻው ሽብሩ - የጤና ቢሮ ኃላፊ
23 አቶ ወገኔ ብዙነህ - የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ሆነው መሾማቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።