የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ከአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ከአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2015 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ጋር ኢትዮጵያ በምትከተለው የገንዘብ ፖሊሲ ላይ ያተኮረ ውይይት አደረጉ፡፡
አቶ ማሞ በባንኩ ዘርፍ እና በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይም መምከራቸውን ከባንኩ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል::
የብሔራዊ ባንክ ገዢው በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ይህ ሪፎርም የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ሥራ ላይ የተሠማሩ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን እንደሚያበረታታም አስገንዝበዋል፡፡
በቀጣይም የባንክ እና የኢንቨስትመንቱ ዘርፍ እየተጠና አስፈላጊ ማሻሻያዎችን ለማድረግ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን አሰርድተዋል፡፡