ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በጤናው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በጤናው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በጤናው ዘርፍ በተለይ በምርምርና አካዳሚክ ስራዎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።
ለዚህም እንዲረዳ የመግባቢያ ሰነዶችን በጋራ ለማዘጋጀት መስማማታቸውም ነው የተገለጸው።
ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ በተለይም በምርምርና አካዳሚክ ስራዎች ላይ ያላችውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱላሂ ሁሴን የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ከፓኪስታን የብሄራዊ የጤና አገልግሎት ቁጥጥርና ማስተባበር ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር በሲር አቻክዛይ እንዲሁም ከፓኪስታን የህክምና ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት በጤናው ዘርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ተቋማዊ ትስስርን መፍጠር ይገባል።
ልዑኩ በኢትዮጵያ ስላለው የጤና አጠባበቅ ስርዓት እንዲሁም በዘርፉ ስለሚሰጡ ስልጠናዎችም ማብራሪያ ሰጥቷል።
ልዑኩ የፓኪስታን ሜዲካል ሳይንስ ኢንስቲትዩትን የጎበኘ ሲሆን ከኢንስቲትዩቱ የስራ ሃላፊዎች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ውይይት አድርጓል።
በተጨማሪም በፓኪስታን የሚገኙ የተለያዩ የህክምና ተቋማትንና የጤና ትምህርት ተቋማትን መጎብኘቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።