ቀጥታ፡

የአፍሪካ ሲንጋፖር ቢዝነስ ፎረም 2023 በሲንጋፖር መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2015 (ኢዜአ)፦የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በጋራ የሚሳተፉበት የአፍሪካ ሲንጋፖር ቢዝነስ ፎረም 2023 በሲንጋፖር እየተካሄደ ይገኛል።

በፎረሙ ኢትዮጵያን በመወከል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ኃላፊዎቹ በቆይታቸው ከተለያዩ አለም አቀፍ አምራቾችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይቶችን እያካሄዱ ሲሆን ይህም ለኢትዮጵያ አዲስ ኢንቨስትመንት በማምጣት በኩል ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ እንደ አንድ ትልቅ የኢንቨስትመንት እድል የተዋወቀ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ የተዘጋጁ መሰረተ ልማቶችና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችም ቀርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም