በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 23/2015(ኢዜአ)፦ በሀንጋሪ ቡዳፔስት በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከዓለም ስድስተኛ ከአፍሪካ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።
ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ 2 የወርቅ ፣4 የብርና 3 ነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ማግኘቷ ይታወቃል።