ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ለምታደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ለምታደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2015 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከግብጽ ጋር ለምታደርገው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ዝግጅት 23 ተጫዋቾች ጥሪ እንደተደረገላቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
በምድብ አራት የሚገኙት የሁለቱ አገራት ጨዋታ ጳጉሜን 3/2015 በግብጽ ይካሄዳል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ፌዴሬሽኑ መልዕክት አስተላለፏል።
በምድብ አራት የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአራት ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ የያዘ ሲሆን ከምድቡ አስቀድሞ መውደቁ የሚታወስ ነው።
በዚሁ ምድብ ግብጽና ጊኒ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸው ይታወቃል።