ቀጥታ፡

ለሁለት ቀናት ሲካሔድ የቆየው የሕዳሴ ግድብን የመጀመሪያ ሙሌትና ውሃ አለቃቀቅ የተመለከተው የመጀመሪያ ዙር ውይይት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2015 (ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የመጀመሪያ ሙሌትና ውሃ አለቃቀቅን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ ልዑካን መካከል ለሁለት ቀናት የተደረገው የመጀመሪያው ዙር የሦስትዮሽ ድርድር ዛሬ መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የልዑካን ቡድኑ ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት በሚደረስበት ሁኔታ ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
 

ሦስቱ አገራት የሦስትዮሽ ድርድሩን በመስከረም 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለማስቀጠል ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ በፍትሐዊ እና ምክንያታዊ መርህ መሠረት የራሷን ድርሻ እና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ድርድሩ በስምምነት እንዲቋጭ ጥረቷን እንደምትቀጥልም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም