በአዲስ አበባ ከተማ በቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረቡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ከተማ በቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረቡ ነው
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 21/2015(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ከተማ በ172 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ስፍራዎች ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቾቸ እየቀረቡ እንደሚገኙ ተገለጸ።
የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያዎች የነዋሪውን የኑሮ ጫና በማቃለል እና የምርቶችን ዋጋ በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ::
ገበያዎቹ ለማህበረሰቡ አማራጭ የመገበያያ ስፍራ ከመሆን ባሻገር የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የፋብሪካ ምርቶችን በቀጥታ ለሸማቹ በማቅረብ ለምርቶች ዋጋ መረጋጋት ብሎም የኑሮ ውድነትን በማቃለል ትልቅ አስተዋፅዖ በማበርከት ላይ ናቸው ፡፡
በአሁኑ ሰዓት 172 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎች በከተማዋ የሚገኙ ሲሆን በሁሉም ቦታዎች ምርቶች ከመደበኛው ገበያ ዝቅ ባለ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረቡ መሆኑን ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡