በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጋምቤላ ከተማ ከ100 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባ ትምህርት ቤት ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጋምቤላ ከተማ ከ100 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባ ትምህርት ቤት ተመረቀ
ጋምቤላ፤ ነሀሴ 21/2015(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጋምቤላ ከተማ ከ100 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የኢፋ ቦሩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
ትምህርት ቤቱን የመረቁት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ናቸው።
በምረቃ ሥነ-ስርአቱ ላይ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።
ዛሬ የተመረቀው ትምህርት ቤት ደረጃውን የጠበቀ የመማሪያ፣ የቤተ ሙከራ፣ የቤተ መጻህፍት፣ የአስተዳደርና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ተገልጿል።