ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ብርሃን ያጡ ወገኖችን ብርሃን እንዲያገኙ እያከናወነ  ያለውን ስራ  አጠናክሮ መቀጠል አለበት-  ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 20/2015 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ብርሃን ያጡ ወገኖችን ብርሃን እንዲያገኙ እያከናወነ ያለውን ስራ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡  

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ የተመሰረተበትን 20ኛ ዓመት "ብርሃን ይስጡ፤ ብርሃን አይቅበሩ" በሚል መሪ ሃሳብ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት አክብሯል። 

በመርሃ ግብሩም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚሁ ጊዜ የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ የበርካታ ዜጎች ብርሃን እንዲመለስ በማድረግ ወገናዊ አልኝታነቱን በተግባር እያሳየ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ባለፉት 20 ዓመታት ለበርካቶች የዓይን ብርሃን መመለስ ከፍተኛ ሚና አብርክቷል፤ በዚህም ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

ይህን ስራም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በ1995 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ከለጋሾች የዓይን ብሌን በመሰብሰብ ብርሃናቸውን ላጡ ወገኖችን በንቅለ ተከላ ማየት እንዲችሉ የሚያመቻች ሰብዓዊ ተቋም ነው።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም