የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 20/2015 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በ1995 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ከለጋሾች የዓይን ብሌን በመሰብሰብ ብርሃናቸውን ላጡ ወገኖችን በንቅለ ተከላ ማየት እንዲችሉ የሚያመቻች ሰብዓዊ ተቋም ነው።