የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ ፈትተን በጋራ እንሻገራለን- አቶ ኡመድ ኡጅሉ - ኢዜአ አማርኛ
የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ ፈትተን በጋራ እንሻገራለን- አቶ ኡመድ ኡጅሉ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 20/2015(ኢዜአ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በዓለ ሲመት በባሕርዳር ከተማ ተካሂዷል። በበዓለ ሲመቱ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የጋምቤላ ክልል ርስሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጅሉ የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ እንፈታለን ብለዋል።
ጠላቶቻችን በየጊዜው አጀንዳ እየሰጡ ከግጭት አዙሪት እንዳንወጣ አድርገዋል ነው ያሉት። በአማራ ክልል የተፈጠረው ችግር እንዳሳዘናቸው እና እንደሚያወግዙት ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ሕዝብ መብቶችና ጥቅሞች ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።
ችግሮቻችን የጋራ መሆናቸውን በማሰብ በጋራ መሥራት ይገባል ነው ያሉት። የጋምቤላ ክልል የአማራ ሕዝብ ወደ ቀደመ ሰላሙ እንዲመለስ አብሮ እንደሚሠራም አረጋግጠዋል። የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ ፈትተን በጋራ እንሻገራለንም ብለዋል። አሚኮ